December 25, 2023
በቅድሚያ እንኳን ለአውሮፓውያን የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ እያልን መጪው አዲስ አመት እና የኢትዮጵያውያን የገና በአል የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።
ኮርፖሬሽኑ አራተኛ ዙር የቦርድ አባላት ስብሰባውን በማድረግ የሽግግር እና የስራ ማሻሻያ እቅዶችን አውጥቷል። አጠቃላይ ጉባኤው በአመታዊ ስብሰባ ያጸደቃቸውን ውሳኔዎችም በፍጥነት የሚፈጸሙበትን እቅድ እየተገበረ ይገኛል። ቦርዱ በእነዚህ ስብሰባዎቹ የደረሰባቸው ውሳኔዎች እና እቅዶች በከፊል እንደሚከተሉት ናቸው።
1ኛ ኮርፖሬሽኑ ለመረዳጃ አባሎቹ የሚከፈለውን የአደጋ ጊዜ ጥቅም ለመክፈል እንዲችል ከአባላቶቹ በአስቸኳይ ውዝፍ እዳዎችን መሰብሰብ እንዳለበት ተስማምቷል። ይህንንም ውሳኔ በቁርጠኘነት ለማስፈጸም እዳ ያለባቸው የኮርፖሬሽኑ የመረዳጃ ማህበር አባላት እስከ January 15, 2024 ድረስ እንዲከፍሉ ያሳስባል ። በጃንዋሪ 15፣ 2024 እዳቸውን ያላጠናቀቁ አባላት በአዲሱ የመረዳጃ ማህበሩ መተዳደርያ መሰረት ከመረዳጃ ማህበሩ አባልነት የሚሰረዙ መሆኑን ቦርዱ ያሳስባል። ከዲሴምበር 26 እስከ ጃንዋሪ 15 ድረስ እዳ ያለባችሁ የመረዳጃ አባላት በሙሉ የቴክስት የኢሜልና የስልክ ጥሪ እንደሚደርሳችሁ በቅድሚያ እናሳውቃለን።
2ተኛ ክፍያቸውን ላጠናቀቁ የኮርፖሬሽኑ አባላት የመረዳጃ ማህበሩ አባልነት መታወቅያና የአክሲዮን ባለቤትነት ሰርተፊኬት ከጃንዋሪ 15 ጀምሮ በጽህፈት ቤታችን መሰጠት ይጀምራል።
3ተኛ አጠቃላይ ጉባኤው በስብሰባ ባጸደቀው መሰረት መረዳጃ ማህበሩ የራሱን የመተዳደርያ ደንብ ኖሮት ስራውን በተቀላጠፈ መልክ በአዲሱ አመት ይጀምራል።
4ተኛ ኮርፖሬሽኑ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ከሶስት መቶ በላይ አዲስ የኮርፖሬሽን አባላት ለመመዝገብ እቅድ አውጥቶ ምዝገባ በዲሲ ሜሪላንድ እና በቨርጂንያ በአዲሱ አመት ይጀምራል። እርስዎም በአዲሱ አመት የሼር ቁጥሮን አጠቃላይ ጉባኤው በተስማማበት መሰረት ቢያንስ ወደ አስር እንዲያሳድጉ እንመክራለን።
5ተኛ የፕሮጀክት ጥናት፣ የኢንቨስትመንት እቅዶችና የመጀመርያው ሶስት ወር የስራ ሪፖርት ላይ ከኮርፖሬሽኑ አባላት ጋር ውይይት እና ምክክር በማርች 31፣ 2024 በዙም (Zoom) የምናካሂድ መሆናችንን በቅድሚያ እናሳውቃለን።
6ተኛ የቦርዱን የስራ ሪፖርቶች፣ ማስታወቅያዎችን ለመመልከት የኢትዮጵያ አንድነት መረዳጃና ልማት ማሕበር (ኮርፖሬሽን) – EUSDA Corp.[/fusion_content_box]
Community-Based Investing
A radical transformation has been taking place over the last year –
How community-based crowdfunding works
AImagine that you know a talented, ambitious chef who wants to open
Neighbors Pool Their Money To Invest In Their Communities
A Cooperative Capital lets people pool small amounts of money, vote on
5 Top Opportunities For Investment In Ethiopia
AThe times are changing in the Horn of Africa and the larger
Shaw-Based Nonprofit Building New Facility In Anacostia
AD.C. nonprofit that provides food and services to those in need is
Ethiopian American Investment Group
Washington region based Ethiopian American Investment group is purchasing a land in